DIRE DAWA ድሬዳዋ
Dirree Dhawaa Diridhaba

Ethiopian Peacemaking Database

In Dire Dawa, we showcase the Mukajela reconciliation system, which translates literally “Under the Shade of a Tree”.

Dire

Name of Reconciliation: Mukajela / Gedkost

Ethnic Group: Oromo & others

About Dire Dawa and Reconciliation Origins: 

ድሬደዋ በኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ምስረታ ጋር ተያይዞ የተቆረቆረች ከተማ ስትሆን ይህም ከአንድ መቶ አስር አመት በላይ ታሪክ ባለቤት ያደርጋታል፡፡ ድሬደዋ በዘጠኝ የከተማ እና 38 የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረች ሰፊ ከተማ ስትሆን እንደ ሱማሌ፣ ኦሮሞ ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ አደሬ እና ወዘተ በርካታ ብሄርብሄረሰቦች በመተሳሰብ እና በአንድነት ተከባብረው ለዘመናት የኖሩባት አሁንም የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ምስራቃዊ ክፍል የምትገኝ የፍቅር እና የመቻቻል ተምሳሌት የሆነች ከተማ ናት፡፡ በድሬደዋ እና አካባቢዋ በሰፊው ማህብሰቡ የሚጠቀምበት የሙከጅላ ወይም ጌድሆስት ባህላዊ የዛፍ ጥላ ስር ሽምግልና ስርአትን የመጥፋት አደጋዎች ከተጋረጡባቸው የእርቅ ስርአቶች አንዱ ነው፡፡ ስርአቱ ድሬድዋ ለዘመናት ለምትታወቅበት የሰላም እና የመቻቻል ተምሳሌትነቷ ትልቅ ሚና ያለው ሲሆን ስርአቱ ተሰሚነት ባላቸው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተደማጭ እንዲሁም ተፅኖ ፈጣሪ በሆኑ ሰዎች መሪነት በዛፍ ጥላ ስር በሚደረግ የውይይት እና የምክክር ሂደት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ሰላምን የመመለስ እና እርቅ የማውረጃ መንገድ ነው ፡፡ ሙከጀላ ከሁለት የኦርምኛ ቋንቋ ቃላት የተዋቀረ ስያሜ ሲሆን ሙካ ማለት እንጨት(ዛፍ) ፤ ጀላ ማለት ደግሞ ስርአጠገብ የሚል ትርጉም ሲኖረው በአጠቃላይም ሙካጀላ ማለት የዛፍ ጥላ ስር የሚል ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጓሜ ይይዛል፡፡

ማጠቃለያ:

ሙከጀላ በማህበረሰቡ መካከል ለሚፈጠረ ማንኛውም ግጭትም ሆነ አለመግባባት በዛፍ ጥላ ሆኖ የሚመከርበት ቀደምት ባህል ነው፡፡ ይህ የዛፍ ስር ውይይት የሚመራው በአካባቢው ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ በሚሰጣቸውና በሚከበሩ ትልልቅ አባቶች ነው፡፡ በአካባቢው የሚኖር ማንኛውም ሕብረተሰብ ክፍልም ታዲያ የአባቶቹን ምክርና ውሳኔ ምንም ይሁን ያከብራል፡፡ የዕርቁ ሂደት የሚካሔድበትን ቀንና ቦታ የሚመርጡት በአካባቢው ውስጥ ባሉት ማህበረሰቡ በመረጧቸው ሽማግሌዎች ወይም አባቶች ነው፡፡ ይህ ዕርቅ ስርዓት የሚጠናቀቀው አባቶች ለፈጣሪ በሚያደርጉት ምስጋና እና ፀሎት ነው፡፡ ባለ ጉዳዮች አባቶችን አክብረው በመምጣታቸው ያሰቡት ሁሉ እንዲሳካላቸው፣ የነኩት ሁሉ እንዲባረክላቸው ይመርቋቸዋል፡፡ “እኛን እንደሰማችሁ ፈጣሪ ፀሎታቹን ይስማ፣ ለሌሎችም አርአያ ናችሁና ተባረኩ” ብለው ይመርቃሉ፡፡ የምሰጋና እና ፀሎቱም ፈጣሪያቸው ፈቅዶ የሽምግልና ስራቸውን አስጀምሮ ስላስጨረሳቸው ፣ ልፋታቸው ፍሬ ስላፈራ እና ሠላም ስለሰፈነ ለፈጣሪ ትልቅ ምስጋና በህብረት ያደርሳሉ፡፡

በመጀመሪያ ግጭት ሲፈጠር በዳይ በድያለሁ ወይም ተበዳይ ተበድያለሁ ሲሉ ዕርቁን ለሚያከናውኑ ሽማግሌዎች አቤቱታቸውን ያቀርባሉ፡፡ ሽማግሌዎቹ ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ ወደ ዛፍ ጥላ ስር የዕርቅ ስርዓት ከመሄዳቸው በፊት በመነጋገር በመወያየት ችግሩ ሊፈታ የሚቻልበትን ሁኔታ በመፍጠር ዕርቅ ለማከናወን ይመክራሉ ነገር ግን አንድ ሰው መግደል እና የጎሳግጭ ትከባድ ችግሮች ሲሆኑ ሽማግሌዎቹ በመነጋገር ቀን ቀጠሮ በመያዝ ይለያያሉ በዚህ መሀከል ዳኝነቱ የሚያከናውኑ ሽማግሌዎች ስለጉዳዩ በቂ የሆነ እውነተኛ መረጃ ያሰባስባሉ የቀጠሮው ቀን ሲደርስ (በአንድ ትልቅ ዛፍ ጥላ ስር) ሽማግሌዎችን ጨምሮ ከበዳይም ከተበዳይም ወገኖች ይሰባሰባሉ፡፡ በዕለቱ በሁለቱም ወገኖች ያሉትን ቅሬታዎችና ሀሳቦች ካደመጡ በኋላ አስቀድመው ካሰባሰቡት መረጃ ጋር በማጣመር በነገሩ ላይ በሰፊው ከተወያዩ በኋላ ውሳኔ ሀሳቦችን ይሰጣሉ፡፡ የሙካጀላ የዕርቅ እና የሽምግልና ስርአት ማህብሰቡ ለራሱ ውስጣዊ ችግሮች ውስጣዊ መፍትሔ ለመስጠት ያቋቋመው እና ልክ እንደትልቅ የፍትሕ ስፍራ የሚታይ ነው፡፡

በድሬደዋ እንደ ሙከጅላ ወይም ጌድኮስት ያሉ ባህላዊ የእርቅ እና የሽምግልና ስርአት ለዘመናት የተኮራረፈን በፍፁም ይቅርታ ሲያስታርቁበት የቆየ የዛፍ ጥላ ስር የእርቅ ስርአት ያላት ሲሆን በዚህም የፍቅር እና የሰላም እንዲሁም ሰው ሁሉ በስብዕናው ብቻ ተከባሮ የሚኖርባት ከተማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ የዚህ ፅሁፍ ትኩረት የሆነው የሙከጅላ የዕርቅ ስርአት በድሬደዋ በከዚራ ፣ ለገሀሬ፣ ገንደቆሬ፣ ገንደገራዳ እና መልካጀብዱ ወዘተ አካባቢዎች በስፋት ሲከናወን የቆየስርአት ሲሆን እንዲሁም እንደሁርሶ፣ ደንገጎ፣ኤረር፣ ሽንሌ እና ጭሮወዘተ አዋሳኝ አካባቢዎችም እንደየማህበረሰቡ ባህል ሲከወን የቆየ የዕርቅ እና የሽምግልና ስርአትነው፡፡ ፡በአሁኑ ዘመን በተለይ በወጣቱ ትውልድ ስርአቱ ስለመኖሩ እንኳን ግንዛቤ የሌለበት እና ግንዛቤ ያለው እንኳን ኋላቀር በሚል አስተሳሰብ በአጉል የዘመናዊነት የተዛባ አመለካከት ተይዞ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ለዚህም ይመስላል ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ከምትታወቅበት ፍቅር እና ሰላም ተምሰሌትነቷ በሚቃረን መልኩ ያልተለመዱ ማህበራዊ ግጭቶች እየተበራከቱባት ያለው፡፡ እንደሀገር ለባህላዊ የእርቅ ስርዓቶች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በት/ት መዋቅሩ ውስጥ እንዲደራጁ ማድረግ መንግስት የተለያዩ ፖሊሲዎችን ሲቀርፅ ለእነዚህ ባህላዊ የዕርቅ ስርአቶች እና ሌሎች አውንታዊ ገፅታ ያላቸውን ባህላዊ እሴቶች ቢያካትት ጥሩ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡ የሙካጀላ የዕርቅ ስርአት ፍፁም የሆነ ይቅርባይነት እና ሰው በሰዋዊማንነቱ ክቡር መሆኑን የሚያሳይ ስርአት ነው፡፡ ይህም ሰውን በሰውነቱ ማክበትና ፍፁም ይቅርባይነትን የማንነትአካልማድረግ ለመልካም ማህበረሳባዊ መስተጋብር እና ለዘላቂ ሰላም ትልቅ መሰረት መሆኑንያ ሳያል፡

 

Click here to read the full research paper (Amharic)